Sunday, April 10, 2016

ምድረ ኢትዮጵያ. A Look at How Ethiopia's Religious History is Cut short for a grabbing partisanism. Alelign A. Wudie

ምድረ ኢትዮጵያ

A Look at How Ethiopia's Religious History is Cut short for a grabbing partisanism


When I was reading a text about St. Mary's and God, Jesus Christ's Visit to Ethiopia, I was very intrigured on a partisan reconstruction of sacred history. Here is my analysis.

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ፡፡ 

ከቀኝ ጎኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል ወይም ይረጫል፡፡ እናቱንም እንዲህ አላት አንቺ በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህ ሀገር ይወለዳሉ፡፡ 

ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ፡፡ ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች፡፡ የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል፡፡ ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው፡፡ First of all, Mary and Jesus Christ came to Ethiopia through indistinguishable palces. Any one can think out of the box. It is God's land. Besides, there is a molested history about Debre Damo. Debre Damo is named after one of the Nine saints who came to Ethiopia ca. 6-8th century. 

ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ፡፡ ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ፡፡ የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት፡፡ የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚል ነበር፡፡ ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ ሄዱ:: This is again a violation of God's and St. Mary's Love to Axumite People. If they went to Aksume Tsion, why couldn't they Reveal Themselves and Bless the People of Aksume? 

በደመና ተጭነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ ፡፡ ጌታም እናቱን እንዲህ አላት ይህች ሀገር እንደ አክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ 

ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /ወደ ዋልድባ / ሄዱ፡፡ በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ ብትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ፡፡ ሦስት መቶ አስራ ስምንት ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት፡፡ እናቱም ይህን የሚመር ዕንጨት አልበላም አለችው፡፡ ጌታም በኋላ ዘመን ስምሺን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ፡፡ ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ Though I appreciate the authority of God on "He can do whatever He wants", this one (the natural fabrications at Waldeba) is totally unacceptable. Yosef could have done it so; otherwise clearly stated, you cannot have a belief system on fabrications. Stop! Think more! Be critical! This is not politics. This is religion. He could have done things in a different way. If this text is meant to encourage hermit life, that could be another interpretation. 

ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ፡፡ በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው ሦስት ወር ከአስር ቀን ተቀመጡ፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም ፡፡ What did They (God, St. Mary and Angels) do at Tsana Lake? Why did the writer jump textual credibility here. This is unjust belief construction for misbelief. 

በጥር አስራ ስምንት /18/ ቀን ዑራኤል መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ፡፡ ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን አሳያት፡፡ (What do you mean by "አሳያት"? Where did they go? How did they go? How long did they took to visit the Mountains? How can he give just Mountains to the Towering Mother St. Mary? That is illogically inconsistent to the Theology and the Theoculture.

እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው፡፡ ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት፡፡ በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞቸን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ በደመና ተጭነው ጥር 29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ፡፡ However, again, in this lines, there are many other interesting stories that God and St. mary Walked and Visited the different Villages of Gondar, Gojjam, Wollo, Oromiya, SNNPR, and the Ethiopia of Ancient period which you might think as the Ethiopia. It was a big kingdom than what we might think. Ponder hard.

ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው፡፡ ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡

ለዚህ ነው እኛ የኢትዮጵያ ልጆች በደማችን ውስጥ ማርያም ማርያም የሚል ስም ያለው:: አሁንም አምላክ ፍቅሯን ያብዛልን አሜን::

Alelign A. Wudie

No comments:

Post a Comment